ሦስተኛው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጥናት ጉባኤ

ጥቅምት ፲-፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም.፤ (አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ)

ጭብጥ፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እና የሀገር ግንባታ

ቁልፍ ተናጋሪዎች (Keynote Speakers)

  1. ክብርት አምባሳደር ዓለምፀሐይ መሠረት– በኡጋንዳ የኢትዮጵያ ባለሙሉሥልጣን አምባሳደር፣ ኡጋንዳ
  2. ፕሮፌሰር ጥላሁንተሾመ – በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ፕሮፌሰር ፣ ኢትዮጵያ
  3. ፕሮፌሰር ሳሙኤል ሩቢንሰን – በሉንድ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ፕሮፌሰር፣ ስዊድን

ዓላማ

ይህ “ሦስተኛው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ጥናት ጉባኤ” የተዘጋጀው በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ የሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የጥናትና ምርምር ክፍል አስተባባሪነት ሲሆን መሪ ቃሉም “የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እና የሀገር ግንባታ” ” የሚል ነው። ጉባኤው የሚካሄድበት ቀን እና አድራሻ  መስከረም ፲ እና ፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም.  በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን የስብሰባ አዳራሽ (አዲስአበባ አምስትኪሎ) ይሆናል።

ጥናቱ የሚቀርብባቸው አውዶች

በጉባኤው ላይ የሚቀርቡ ጥናታዊ ጽሑፎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለሀገር ግንባታ ያደረገችውን ሚና እና ተያያዥ ጉዳዮች የሚያሳዩ ሆነው በሚከተሉት የጥናት ዐውዶች ዙሪያ እንዲሆኑ ይፈለጋል፤

  • የአብነት ትምህርት ለሀገር ግንባታ ያለው ቁልፍ ሚና
  • ሀገራዊ ስሜት እና የቤተክርስቲያን ሁሉንም የማስተባበር መንፈስ
  • በብሔራዊ ቀውስ ጊዜ የቤተ ክርስቲያን ሚና
  • ሥልጣንን በአግባቡ መጠቀም እና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን
  • የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እና ሀገራዊ የግብረ ገብነት እሴቶች
  • በብሔራዊ እርቅ እና መግባባት ቤተ ክርስቲያን የሚኖራት ሚና
  • የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እና ማህበረ-ምጣኔሀብታዊ ለውጥ
  • እምነት እና ፖለቲካ በአሁኗ ኢትዮጵያ
  • ብሔራዊ አሻራዎች (ምልክቶች) እና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን
  • የቤተ ክርስቲያን ሚና በመንግሥት እና ሕዝብ መካከል

በዚህ ዝርዝር ላይ ያልተካተቱ ሌሎች ከጉባኤው ዓላማ ጋር የሚሄዱ ርእሶችም ሊቀርቡ ይችላሉ።

የጽሑፍ አጠቃሎ ማቅረቢያ

የጉባኤው አዘጋጆች የተለያየ ሙያ ያላቸው ምሁራንን ጥናታዊ ጽሑፍ እንዲያቀርቡ እየጋበዙ የጽሑፍ አጠቃሎአቸውን ከ450 ቃላት ባልበለጠ አዘጋጅተው እንዲልኩ ይጋብዛሉ። በቀረበው የአጠቃሎ ጽሑፍ ብስለት እና ጥራት መሠረት ምርጫ ተደርጎ ያለፉት ርእሶች ይፋ ይሆናሉ። አቅራቢዎች ከሚልኩት የጽሑፍ አጠቃሎ በተጨማሪ ሙሉ ስማቸውን እና የሚሰሩበትን ወይም የሚያገለግሉበትን ተቋም ከ“ግለ-ታሪክ”(CV) ጋር የሚገኙበትን አድራሻ አካተው በአንድ ገጽ እንዲልኩ ይጠየቃሉ። የተመረጡት የጽሑፍ አጠቃሎዎች በመጽሔት መልክ ታትመው በጉባኤው የሚሠራጩ ሲሆን በጉባኤው ላይ ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው እና መመዘኛውን የሚያሟሉ የጥናት ወረቀቶች በ“የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጥናት መጽሔት” (Journal of Ethiopian Church Studies) እንዲታተሙ ይላካሉ። የጽሑፍ አጠቃሎዎችን (Abstracts) እና ጥናታዊ ጽሑፎችን በዚህ የኢሜይል አድራሻ  research@eotcmk.org  ይላኩልን።

ቋንቋ

ጉባዔው በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች የሚካሄድ ስለሆነ ጽሑፍ አዘጋጆች ከሁለቱ በአንደኛው ቋንቋ ጽሑፋቸው ማቅረብ ይችላሉ።

የጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ አባላት

  • ቀሲስ ዶ/ር መንግሥቱ ጎበዜ – ሰብሳቢ
  • ቀሲስ ዶ/ር አምሳሉ ተፈራ – ም/ሰብሳቢ
  • ዶ/ር ዮሐንስ አድገህ – ጸሓፊ
  • ዶ/ር ፍሬሕይወት ባዩ – አባል
  • ዶ/ር ሶስና መንግሥቱ– አባል
  • ዶ/ር ወለላ አበሆዴ – አባል
  • ዶ/ር ዮናስ አሽኔ – አባል
  • ዶ/ር ዘርአየሁ ስሜ – አባል

ድረ ገጽ ዝግጅት

  • ዲ.ን ዓለምነው ሽፈራው

ያግኙን

ኢሜይል: research@eotcmk.org

ትኩረት የሚሰጣቸው ቀኖች

የጽሑፍ አጠቃሎ ለማስረከብ = እስከ ነሐሴ ፱ ቀን ፳፻፲፩ ዓ.ም.
የተመረጡ ጥናቶች ይፋ የሚሆኑበት = ነሐሴ ፳፬  ቀን ፳፻፲፩ ዓ.ም.
ጉባኤው የሚካሄድባቸው ቀናት =መስከረም ፲ እና ፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም.